Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ዩኒቨርሲቲና ስፔስ ሣይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና የጥናት ፕሮጀክት ሥራ ለመሥራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፣ በጋራ የምርምርና የጥናት ፕሮጀክት ሥራ ለመሥራት የኮንትራት ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱ ሀገር በቀል ተቋማት ወቅቱ የሚጠይቀውን የወታደራዊ ሣይንስና ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ነው ስምምነት የደረሱት ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኮማንዳንት ተወካይ ኮ/ል ገዛኸኝ ፈቃዱ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ተፈራርመዋል።

ኮ/ል ገዛኸን ፈቃዱ ፥ በሀገር ላይ የሚደረጉ ተፅዕኖዎችን ለመመከት ጠንካራ ኢኮኖሚና የመከላከያ ኃይል መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፥ ትብብሩ ኢትዮጵያ በሳተላይት መስክ የጀመረችውን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና እንደ መከላከያ ተቋም ደግሞ ዘመናዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ለመታጠቅ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አብዲሳ ይልማ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ካለችበት የጂኦፖለቲካ አንፃር ዘመኑ የሚጠይቀውን ወታደራዊ ቴክኖሎጂ መታጠቅ አስፈላጊ በመሆኑ በትብብር መሥራት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሣይንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ በሚያስጀምረው የኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ኢንሰቲትዩት የድህረ ምረቃ ትምህርት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እንደሚያሳትፍ ማሳወቁን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.