Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የንባብ ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ንባብ ባህላችን እናድርግ ” በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ዛሬ ጥር 4 የንባብ ቀን ሆኖ እየተከበረ ነው።
ከዚህ በኋላ በክልሉ ወር በገባ አራተኛው ቀን የንባብ ቀን ሆኖ ይውላልም ነው የተባለው፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ማንኛውም ሰው የማንበብ ባህሉን እንዲያዳብር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የማንበብ ባህል በተለይም ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እየዳበረ እንዲሄድ የተለያዩ ውድድሮች እና እንቅስቃሴዎች መደረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
የንባብ ቀን መርሃ ግብር በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል፣ በዞኖች፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በወረዳዎች እንደሚደረግ ከኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.