Fana: At a Speed of Life!

በቀጣናው የሰላምና የመከባበር ዕሴትን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ አፍሪካ የቀጠናውን የሰላምና የመከባበር ዕሴት ለመገንባት እንዲሁም ጽንፈኝነትን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤና የኬንያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ናቸው።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትና የኬንያ የተቋሙ ዳይሬክተርና ዋና ጸሐፊ ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት ለአገራዊና አካባቢያዊ ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል።

ስምምነቱ የሁለቱ ሀገራት በጋራና በትብብር የመስራት አካል ነው የተባለ ሲሆን÷ ወደፊትም በቀጠናው ካሉ አገራት ጋር ይህ ግንኙነት እንደሚጠናከር ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ ስምምነቱ ትውልድን በበጎ ለመገንባትና የዕርቀ ሰላም አጀንዳዎችን ለማስፈጸም እንደሚያስችል መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.