Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ መካከለኛ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ብድር መተግበርያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ መካከለኛ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ “ሚቹ” የተባለ የዲጂታል ብድር መተግበርያ ይፋ አደረገ።

በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ የቀረበው ይህ የብድር መጠየቂያ እና ማግኛ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የመጀመርያው መተግበሪያ ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ደርቤ አስፋው እንዳሉት፥ “ሚቹ” ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ማስያዥያ የማይጠየቅበት የዲጂታል ብድር መተግበሪያ ነው ፡፡
ለመካከለኛ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ማመልከቻ መመዘኛና እና ማቅረብያ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊና ፈር ቀዳጅ የብድር መተግበሪያ መሆኑም ተገልጿል።

በባንኩ የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥቃቅን ንግድ ስራዎች ብድር መንገድ ዳር የሚከናወኑ እና ጥቃቅን የንግድ ስራዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ፥ የአነስተኛ እና ኢንተርፕራይዞች ብድር ደግሞ በአነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ነጋዴዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።

በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙኒር ዱሪ የ”ሚቹ “ተጠቃሚዎች ብድር ማመልከት እንዲችሉ መስፈርቱን በማሟላት የብድር ምዘና እና የግምገማ ሂደት እንዲሁም አፀዳደቅና አሰጣጥ በዲጂታል ስልት በአጭር ጊዜ የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

በቅድስት ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.