Fana: At a Speed of Life!

የወንጌላውያን ህብረት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጌላውያን ህብረት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከበ::

ህብረቱ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአማኞች የተሰበሰበውን 10 ሚሊየን ብር ነው በዛሬው እለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስረከበው፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የዘፀዓት ቤተክርስቲያን መሪ ፓስተር ዩሃንስ ግርማ ÷ የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ስለኢትዮጵያ ጥሪ የበኩላችንን ምላሽ ለመስጠት በርካታ ምእመናን በነቂስ በመሳተፍ ለወገኖቻቸው ያላቸውን አጋርነት ያላቸውን በማዋጣት አሳይተዋል ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፥ የተጎዱ ወገኖቻችንን በአንድነት ማቋቋም ይገባል በማለት የከተማ አስተዳደሩ ይህን ተግባር የሚመራ አንድ ግብረሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውሰው ይህንን ጥሪ ሰምተው ምላሽ የሰጡትን የወንጌላውያን ህብረት አመስግነዋል፡፡

የከተማው አስተዳደርም የጀመረውን ተጎጂዎችና ተፈናቃዮችን የማቋቋም ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውንም ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.