Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ የደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን እና በተላላኪው ኦነግ ሸኔ የደረሰውን ጉዳት ተመለከተ።

ልዑኩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ያካተተ ሲሆን ፥ የሃይማኖት አባቶች በስፍራው ለተገኘው ልዑክ አሸባሪዎቹ አካባቢውን በወረራ ይዘው በነበሩበት ወቅት ያደረሱትን ጉዳት አስረድተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በብሔረሰብ አስተዳደሩ በመዘዋወር የተመለከቱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ፥ የጤና ተቋማት እና የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባቸውም ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጋቸውን አድንቀዋል።

በቀጣይም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው ፥ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የወደሙ ሃብቶችን መልሶ ለመገንባት ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ አስረድተዋል።

የደረሰውን ጉዳት ከመስክ ጉብኝት በተጨማሪ በፎቶ አውደ ርዕይና በዘጋቢ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ለእይታ መቅረቡን አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.