Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ህዝብ ለሃገራዊ እና ክልላዊ ግብ በጋራ ሊቆም ይገባል- የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝብ ልዩነትን የሚያሰፉ ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው ለሃገራዊ እና ክልላዊ ግብ በጋራ ሊቆም ይገባል ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ወጌሾ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቤንች ሸኮ ዞን የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን÷ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትም የክልሉ ህዝብ ከከፋፋይ ሀሳብ ወጥቶ በጋራ መቆም ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በክልሉ ያለው ሃብት ከቀጠናው አልፎ ለሀገሪቱ እንደሚተርፍ የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የህዝቡ ጥያቄ መልስ ማግኘት እንዲችል በጋራ መቆም ይኖርብናል ብለዋል፡፡

“ተሰሚነት እና አቅም የሚኖረን በጋራ ስንቆም ነው፣ ልዩነታችንን መጠቀሚያ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት ሳንጋለጥ ሌብነትንም በመፀየፍ ክልሉን ለማሳደግ በጋራ መስራት ይኖርብናል” ነው ያሉት፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በቤንች ሸኮ ዞን ተገኝተው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በተስፋየ ምሬሳ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.