Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በአሚበራ ወረዳ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የተመራ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ልዑክ በኢንቨስተር እና በአርብቶ አደር ማህበረሰብ እየለማ የሚገኘውን የአሚበራ ወረዳ የስንዴ ማሳን ጎብኝቷል።
 
አቶ አወል አርባ “ምንም እንኳን ክልሉ አሸባሪው ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ እና ጥቃት እየመከተ ቢሆንም ልማቱ እንዳይቋረጥ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል” ብለዋል።
 
ክልሉ በአሁን ወቅት በመስኖ እርሻ ልማት በስንዴ እና በመሳሰሉት እጅግ በጣም አበረታች እና አመርቂ ውጤቶችን በተጨባጭ እያስመዘገበ መሆኑንም አንስተዋል ።
 
በቀጣይ የሚጠበቅብን የመስኖ ልማት ስራ በሚፈልገው ደረጃ የማስፋት ስራ ከኢንቨስተሩ፣ ከአርብቶ አደሩ እና ከከፊል አርብቶ አደሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡
 
የአሚበራ ወረዳ አስተዳደር አቶ አብዱ አሊ በበኩላቸው፥በወረዳ ደረጃ ባለሀብቱ እና ከፊል አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በ2014 ዓ.ም 1 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ያመርታሉ ተብሎ መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡
 
ከዚህ ውስጥም በ1 ሺህ 257 ሄክታር መሬት ስንዴ ማልማት መቻሉን ገልጸው፥ይህም ጥሩ ስኬት እንደሆነ ማብራራታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.