Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ ከአምባሳደሮች ጋር መከረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር መከረ።

 

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ለአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ለጉባኤው እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ማብራሪያ ተሰጥቷል።

 

ለጉባኤው ስኬት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ነገሮች ከማዘጋጀት ባለፈ የተሳታፊዎች ጤንነት መጠበቅን ለማረጋገጥ የኮቮድ-19 ምርመራ እና ክትባት መስጫ የጤና ማእከላት በመንግስት መቋቋማቸውን ነው የገለፀው።

 

አፍሪካውያን ወንድም አህቶች በክፉም ሆነ በደጉ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን በማረጋገጣቸው ሚኒስቴሩ ምስጋናውን በመግለፅ ይኸው ይቀጥል ዘንድ ጠይቋል።
ኢትዮጵያ እንደ አስተናጋጅ ሀገር አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንደተመለደው ከወዲሁ በማጠናቀቅ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ ላይ እንደምትገኝም ነው የተገለፀው።

 

የኮቪድ-19 በስብሰባው ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል አስፈላጊ ዝግጅት መከናወኑንም አብራርተዋል።
በተጨማሪም ሌሎች ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ የሎጀስቲክ አቅርቦቶች ዝግጅት መጠናቀቁም ነው የተገለፀው

 

ለጉባኤው በስኬት መጠናቀቅ ይረዳ ዘንድም አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶቹ የየሀገራቸውን አስፈላጊ መረጃዎች በጊዜ እንዲያቀርቡ ተጠይቋል።

 

ተሳታፊ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በበኩላቸው የተለያዩ ገንቢ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

 

በመጨረሻም በውይይቱ የተሰጡ ግብዓቶችን በመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተሳካ ጉባኤ እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ለተሳታፊ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች አረጋግጧል።
 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.