Fana: At a Speed of Life!

ሕብረት ባንክ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ሕብር ታወር እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረት ባንክ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ አስመረቀ።
የምረቃ መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የባንኩን ህንፃ በይፋ መርቀዋል።
ከተቋቋመ 23 ዓመታትን ያስቆጠረው ሕብረት ባንክ አዲስ ያስገነባው ህንፃ፥ በ3 ሺህ 300 ካ.ሜ ላይ ያረፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ህንጻው ዓለም ዓቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ አገልግሎቶችን በሚሰጡ ቁሳቁሶች የተደራጀ ሲሆን፥ በኮምፓስ የሚሰሩ 13 አሳንሰሮች፣ ከ147 በላይ የደህንነት ካሜራዎች፣ ባለ 270 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ ስክሪን፥ በአጠቃላይ ሁለገብ እና የተሟላ አና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ህንጻ መሆኑ ተገልጿል።
በቆንጂት ዘውዴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.