Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ጥሪዉን ተቀብለው ወደ ሲዳማ ክልል ለመጡ ዲያስፖራዎች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሲዳማ ክልል ለመጡ የዳያስፖራ አባላት አቀባበል ተደረገ።
ከአቀባበል ስነ-ስርዓቱ በተጨማሪ ስለቀጣይ ቆይታቸውና በክልሉ ማግኘት ስለሚችሉት አገልግሎትና የኢንቨስትመንት አማራጮች ምክክር ተደርጓል።
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፥ ያለፉት ሶስት አመታት ኢትዮጵያዊነት የተገነባበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።
የሀገር ህልውናን በማስጠበቅ ዘመቻው ከመከላከያና ከተፈናቃዮች ጎን በመሆን ደጀንነቱን አሳይቷል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ያሸነፈችው አንድ በመሆናችን ነው ያሉት አቶ ደስታ፥ ለዚህም “ከሀገር ውጪ ሆናቹ ከሀገራቹ ጎን መሆናችሁን በተለያየ መልኩ የገለፃችሁ አሁንም የሀገርን ጥሪ ሰምታችሁ የመጣችሁ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ ያላችሁ” ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ጦርነቱ አሁንም እንዳለ በመግለፅ፥ መደጋገፉ ከቀጥለ አሁንም እናሸንፋለን ነው ያሉት።
ኢንቨስትመንትን በማምጣት፣ ቴክኖሎጂን በማሸጋገርና ክልሉን በማስተዋወቅ ስራ ላይ ዳያስፖራው እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.