Fana: At a Speed of Life!

በግጭት ወቅት የተፈፀሙ ወንጀሎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በሽግግር ፍትህ ጭምር ማየት ይገባል- መዓዛ አሸናፊ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭት ወቅት ወይም ከግጭት በኋላ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከመደበኛው የፍትህ ስርዓት ባለፈ በሽግግር ፍትህ ጭምር በማየት የፍትህ ስርዓቱን ለማረጋጋት ስራ ወሳኝ ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ ጠቆሙ።
የፍትህ ስርዓቱ ግጭቶች ሲከሰቱና ከተከሰቱ በኋላ ሊኖረው በሚችለው አዎንታዊ ሚና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
“ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትህ ግጭቶች ሲከሰቱና ከግጭቶች በኋላ” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ባለው ውይይት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ያማከለና አስፈላጊ እንደሆነ በመድረኩ ተጠቅሷል።
በተለይም ውይይቱ በሽግግር ወቅት ስለሚያስፈልገው የሽግግር ፍትህ አተገባበርና ይህንኑ ከመደበኛው ፍትህ ጎን ለጎን ማስኬድ በሚቻልበት አግባብ ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ እየተመራ ባለው የውይይት መድረክ ላይ፥ የአፋርና አማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ከዳያስፖራው ማህበረሰብ የተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎችና የሕግ ምሁራን እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.