Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መምጣት ሳያስፈልገው በሀገሩ መዋዕለ ነዋዩን እንዲያፈስ ምቹ አሠራሮች ይዘረጋሉ – ምክር ቤቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተለያዩ የውጭ አገራት ከመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለመስራት እየመከረ ነው።
በውይይቱ የምክር ቤቱ የቀድሞ እና የአሁን አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ እና ዳያስፖራዎች ተሳትፈዋል።
ዳያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መምጣት ሳያስፈልገው ባለበት ሆኖ በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ እና ምቹ አሰራሮች እንዲዘረጉ ምክር ቤቱ እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልጿል።
አሰራሩን ለማዘመን እና የተሻለ አሰራር ለመተግበር የሚያስችለውን አዲስ ያዘጋጀውንና የሚመራበትን ፖሊሲ ምክር ቤቱ አስተዋውቋል።
ፖሊሲው የምክር ቤቱን ብቻ ሳይሆን የንግድ ተዋንያንንም ቀላል እና ፈጣን አሰራር ለመተግበር አስቻይ መሆኑ የተነሳ ሲሆን÷ ዳያስፖራው በዚህ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሰራር መዘርጋቱም ተመላክቷል፡፡
ዳያስፖራው በቀጣይ ከንግድ ምክር ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን አሰራር ለማወቅ ጥያቄዎችን፣ መረጃ እና አስተያየቶችን ሰንዝሯል።
በቀጣይ የውይይት መድረኮችን በተለያየ መንገድ ከዲያስፖራው ጋር እንደሚያዘጋጅ ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
ዳያስፖራው በሃገር ለማልማት የሚያስችል እቅድ እና ዝግጅት ሊኖረው እንሚገባ ጠቁሟል።

   በፍሬህይወት ሰፊው

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

0
People reached
8
Engagements
Boost post
7
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.