ታዳጊዋ ኢክራም የመኖሪያ ቤት እና የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገላት
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች በቡድን የመደፈር ጥቃት ለደረሰባት ኢክራም ያሲን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት እና አቶ በላይነህ ክንዴ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉላት።
ኢክራም አካላዊ ጉዳት ቢደርስባትም፥ የውስጥ ጥንካሬዋ ለሌሎች ሴቶች ምሳሌ ነው ብለዋል።
“የኢክራም የውስጥ ጥንካሬ ለሌሎች ሴቶች ምሳሌ ነው፤ አካላዊ ጉዳት ቢደርስባትም በመንፈሷ ጠንካራ ናት” ብለዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ባለሃብቶች እንደነ አቶ በላይነው ክንዴ ያሉትም ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የቤት ቁልፍና የ1 ሚሊየን ብር ድጋፉን ቤተሰቦቿ በተገኙበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የበላይነህ ክንዴ ግርፕ መስራች እና ባለቤት አቶ በላይነው ክንዴ አስረክበዋል።
“ታዳጊዋ ኢክራም ትምህርቷን እስከምትጨረስ ድረስ ድጋፋችን አይለያትም” ያሉት አቶ በላይነህ ክንዴ፥ በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ሙሉ በሙሉ መርዳት ባይቻልም ለተመረጡ ወገኖቻችን ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
እስካሁንም በአማራ ባለሀብቶች ጥምረት ጉዳት ለደረሰባቸው እና ጀብድ ለፈፀሙ አራት ቤተሰቦች ድጋፍ መደረጉን ነው የጠቀሱት።
በሌላ በኩል አባቱ በጦርነቱ ለተሰዋበት ህፃን ቢኒያም ጌታቸው ሞሮዳ በአማራ ባለሃብት ጥምረት የ1 ሚሊየን ብር ድጋፋ ተደርጎለታል።
የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ተወካይ አቶ አለነ አድማሴ ለመቶ አለቃ ጌታቸው ሞሮዳ ልጅ ለህፃን ቢኒያም ጌታቸው ሞሮዳ 1 ሚሊየን ብር አስረክበዋል።
ለህፃን አባቢያ ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት መስጠቱ ይታወሳል።
በዙፋን ካሳሁን እና በምንይችል አዘዘው