Fana: At a Speed of Life!

በተመድ የሚደገፈው የሊቢያ መንግስት ከሰላም ድርድሩ መውጣቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተመድ የሚደገፈው የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር ከጄኔቫው የሰላም ድርድር መውጣቱን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፋይዝ አል ሳራጅን አስተዳደር እና ጄኔራል ከሊፋ ሃፍጣርን በስዊዘርላንድ ጀኔቫ እያደራደረ ይገኛል።

ትናንት የከሊፋ ሃፍጣር ታማኝ ሃይሎች በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ በሚገኘው ወደብ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎም የፋይዝ አል ሳራጅ አስተዳደር ከሰላም ድርድሩ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል።

በጥቃቱ በወደቡ በሚገኝ ነዳጅ ማጣሪያ አቅራቢያ ከባድ ፍንዳታ ተከስቷል።

ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ የነዳጅ ኩባንያ ሁሉም የነዳጅ ታንከሮች ከአካባቢው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ሃገራት ለጉዳዩ እልባት እስከሚሰጡት ድረስም ወደ ሰላም ድርድር እንደማይመለስ ነው በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው።

ጥቃቱም በዋና ከተማዋ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራልም ብሏል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.