Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በጎንደር በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ፡፡
 
የጥምቀት በዓል በጎንደር በጥምቀተ ባህሩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከበረ ።
 
በበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች ታድመዋል፡፡
 
በተጨማሪም የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የደብር አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡
 
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር በዓል ነው፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.