Fana: At a Speed of Life!

ጥምቀትን በጎንደር ማክበር የተለየ ደስታ እና ስሜት አለው – ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥምቀትን በጎንደር ማክበር የተለየ ደስታ እና ስሜት አለው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ ገለጹ።
 
ጎንደር ያላትን ባህል እና ቅርስ በሚገባ ከተጠቀመች በቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደምትችል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
 
ጥምቀት በድምቀት የሚከበርበት ባህረ ጥምቀት ያለማንም ፍቃድ በቀደመ ስያሜው የአጼ ፋሲለደስ ባህረ ጥምቀት ተብሎ እንዲጠራም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
 
በበቃ ዘመቻ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖን ላሳደሩ ዳያስፖራዎች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ጥምቀትን በሳላማዊ እና በተለየ ድባብ ማክበር መቻሉ ለዓለምአቀፍ ማህበረሰብ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ እንደሆነም ነው ዶክተር ይልቃል የተናገሩት።
 
ኢትዮጵያውን ትብብርን ማስቀደም ከቻሉ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉም አሁን ያለው ሁኔታ አሳይቷልም ብለዋል።
 
በጥምቀተ ባህሩ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በበኩላቸው፥ የጥምቀት በዓልን ለመታደም በስፍራው የተገኙ እንግዶችን አመስግነዋል።
 
በ#nomore ዘመቻ እና ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ጥሪን ተቀብለው በጎንደር ለታደሙ ዳያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው በጎንደር ለተገኙ የኤርትራ እና የእስራኤል አምባሳደሮችም ምስጋና አቅርበዋል።
 
በጎንደር ከተማ እየተከበረ ባለው የጥምቀት በዓል የማዕከላዊና የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዮሐንስ የኦሃዩና የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አብነ ሰላመ ተገኝተዋል።
 
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኝሁ ተሻገርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.