Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ ሀዋሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢህ አብዲ የተመራ ልዑክ ሀዋሳ ገባ።
 
ልዑኩ ዛሬ ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
የልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.