Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ኑሆ ጎበና የቀብር ሥነ-ስርዓት በአዳማ የሙስሊም መካነ-መቃብር ተፈፀመ።

ለአርቲስቱ አስክሬንም በአዳማ ከተማ ስታዲየም አሸኛኘት ተደርጎለታል።

በዚህም የአሸኛኘት ሥነ-ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ፣ የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሰአዳ አብዱራህማን፣ አባ ገዳዎች፣ የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ እንዲሁም የአርቲስቱ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ተገኝተዋል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና በሙዚቃዎቹ ለሰብዓዊ መብት የሚቆረቆር የማኅበረሰብ አንቂ እንደነበርም ተመልክቷል፡፡

ኑሆ ጎባና በድሬዳዋ ከተማ ካፊራ ጋራ ቀበሌ ከአባቱ መሀመድ ጎበና እና ከእናቱ ፋጡማ አዳም በ1940 ነው የተወለደው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.