Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የህወሓት የሽብር ቡድን አሁንም ትንኮሳውን መቀጠሉን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ክልላዊ ዳይሬክር ሚካኤል ጆን ደንፎርድን ጋር ተወያዩ ።
በውይይቱ ወቅትም የህወሓት የሽብር ቡድን በአፋር እና አማራ ክልሎች በፈጸመው ወረራ በርካታ የሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን አምባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል።
መንግስት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለው ግጭት እንዲቆም ባለው ፍላጎት ሰራዊቱን ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ መወሰኑን አምባሳደር ሬድዋን አብራርተዋል።
ነግር ግን የህወሓት የሽብር ቡድን አሁንም ግጭቱን ለመቀጠል ባለው ፍላጎት የተነሳ ትንኮሳውን መቀጠሉንም ነው የገለጹት።
በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተም የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ክልሉ የገቡ ተሽከርካሪዎችን ህወሓት ለሰራዊቱ ማጓጓዣነት ማዋሉን አስታውሰው፥ ተሽከርካሪዎቹ መመለስ እንዲችሉ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ስለመሆኑም አስታውሰዋል።
አክለውም የዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ ጉዳዩን በዝምታ በማለፉ በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ ችግር መፍጠሩን ነው የገለፁት።
መንግስት የፍተሻ ኬላዎች ቁጥርን በመቀነስ፣ የሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብ የተሰማሩ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ይዘውት የሚገቡትን የጥሬ ገንዘብ መጠን በማሳደግ እንዲሁም በአየር የሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታ በረራ መጠንን በጨመር ቁርጠኝነቱን ማረጋገጡን አምባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል መንግስት የዜጉቹን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊት ያለበት በመሆኑ አሸባሪው ኃይል ትንኮሳውን እስካላቆመ ድረስ ተገቢው እርምጃ መውሰድ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም የሚወሰዱ እርምጃዎች ንጹሃንን ዒላማ ያደረገ ስለመሆኑ ከቡድኑ የሚወጡ መረጃዎች ተጨባጭነት የሌላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሚስተር ሚካኤል ጆን ደንፎርድ በበኩላቸው፥ መንግስት ለተከተለው የሰላም መንገድ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፥ በአንጻሩ ህወሓት በአባላ በኩል የከፈተው ጥቃት ችግሩን እያወሳሰበው መሆኑን አንስተዋል።
ድርጅታቸው 700 ቶን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ለማድረግ መዘጋጀቱን ጠቁመው ፥ በአፋር እና አማራ ክልሎች እርዳታ ለሚሹ ወገኖችም ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩልም በኢትዮጵያ፣ ኬንያና እና ሶማሊያ የድርቅ ተጎጂዎችን ለመርዳት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ጥረት እያደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
በመጨረሻም ሕወሓት የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው ለሚያደርገው ግጭትን የማስፋፋት ተግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተጠያቂ ሊያደርገው እንደሚገባ በውይይታቸው መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.