Fana: At a Speed of Life!

“አንድ ዳያስፖራ ለአንድ ቤተሰብ” ንቅናቄን የተቀላቀሉ የዳያስፖራ አባላት በቅርቡ ቤተሰቦቻቸውን ይረከባሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አንድ ዳያስፖራ ለአንድ ቤተሰብ” የሚለውን ንቅናቄ የተቀላቀሉ በርካታ የዳያስፖራ አባላት በቅርቡ የሚደግፏቸውን ቤተሰቦች እንደሚረከቡ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ።

ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ÷ የዳያስፖራ አባላቱ የሽብር ቡድኑ በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ያወደማቸውን መኖሪያ ቤቶችና መገልገያ ንብረቶች ለመተካት በሃላፊነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ብለዋል።

በመሆኑም የዳያስፖራ አባላቱ በቅርቡ ከሚያቋቁሟቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበትና ሥራቸውን የሚጀምሩበት መርሃ ግብር ይካሄዳል ብለዋል።

ይህ መልካም ተሞክሮ ለዳያስፖራው ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ያሉት ሚኒስትሯ ÷ በሀገር ውስጥም አቅም ያላቸው በጎ ፈቃደኞች ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ሙሉ ቤተሰብ ማቋቋም ባይችሉ እንኳን ‘አንድ ልጅ ለአንድ ወገን’ የሚለውን ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።

ይህኛው ንቅናቄ አንድ ታዳጊ ሕጻን በሃላፊነት መርዳትና ማገዝ የሚያስችል ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት የደረሰባቸውን የሥነ-ልቦና ጫና ማቃለልና አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላትን ያካትታል ብለዋል።

ይህ ተግባር ለሀገር ግንባታ አስተዋጽኦ ከማበርከት ባሻገር ሁሉም ዜጋ በዚህ ረገድ የሚቻለውን እንዲያደርግ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.