Fana: At a Speed of Life!

ከእብናት ወደ ሰቆጣ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ እስካሁን የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከእብናት ወደ ሰቆጣ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአማራ ክልል ትራፊክ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
 
አደጋው የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ አውቶብሱ በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው ተብሏል፡፡
 
የአማራ ክልል ትራፊክ ፖሊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ በደረሰው አደጋ እስካሁን የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ 6 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል፡፡
 
የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.