Fana: At a Speed of Life!

በመስኖ ግድብ ግንባታ የተሰማሩ ተቋራጮች ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካዎች እንዲወስዱ መግባባት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖ ግድብ ግንባታዎች እንዳይቆራረጡና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ተቋራጮች ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካዎች እንዲወስዱ ማድረግ የሚያስችል መግባባት ከአምራቾች ጋር መደረሱን የማዕድን ሚኒስትር ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ÷ በቆላማው የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚደረጉ የመስኖ ግድብ ግንባታዎች ያለባቸውን የሲሚንቶ እጥረት በተመለከተ ከመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መህመድ ጋር በመሆን ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም ፥ የመስኖ ግድብ ግንባታዎች እንዳይቆራረጡና በተገቢው ፍጥነት እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ግንባታውን የሚያከናውኑ ተቋራጮች ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካዎች እንዲወስዱ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከአምራቾቹ ጋር  መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.