Fana: At a Speed of Life!

በበልግ ወቅት የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል

በበልግ ወቅት የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል
 
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበልግ ወቅት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተገለፀ፡፡
 
የብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት የመጪውን የበልግ ወቅት የአየር ሁኔታ አዝማሚያ ትንበያ ይፋ ያደረገ ሲሆን፥ የበጋ ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ ግምገማም አካሄዷል።
 
በመድረኩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከአየር ፀባይ ጋር በተያያዘ የሚሰጡት መረጃዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ እንደ ጎርፍና ድርቅ ያሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከልና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፥መረጃዎቹ የሰዎችን ሕይወትና ንብረት የሀገርን ኢኮኖሚ ከጉዳት በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
 
ከኃይል አቅርቦትም ጋር በተያያዘ መረጃዎቹ የጎላ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
 
በመድረኩ ላይ በቀረበው የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቆላማ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡
 
በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛ ከመደበኛ በላይ፣ የሰሜን ምስራቅ ፣ የመካከለኛውና የምስራቅ እንዲሁም የደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢች ደግሞ በአመዛኙ መደበኛ የሆነ ዝናብ ሊያገኙ እንደሚችሉ በትንበያው ተመልክቷል፡፡
 
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የአየር ሙቀት ከመደበኛው አንጻራዊ ጭማሪ እደሚኖረው ትንበያው ማመላከቱን ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.