Fana: At a Speed of Life!

ህወሃት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደኋላ ለመመለስ ተገደዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ መቀሌ ሲጓዙ የነበሩ  የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸው ተገለፀ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ ህወሃት በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው ትንኮሳ እና ወደ መኖሪያ አካባቢዎች ላይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በዚህ ትንኮሳው እና በፈጠረው የደህንነት ስጋት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ላይ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳልቻሉና ከግማሽ መንገድ በኋላም ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸውን ነው ያመለከተው።

ይህ የህወሃት ድርጊት የሽብር ቡድኑ ለአደገኛ የፖለቲካ ቁማር ሲል ሰላማዊ ህዝብን ለረሃብ እየዳረገ መሆኑን የሚያሳይ ሁነኛ ማስረጃ መሆኑን ጠቁሟል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.