Fana: At a Speed of Life!

11ኛው ሀገር አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው ሀገር አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስ ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባኤው የኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩት ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ጋር በትብብር ያዘጋጀዉ መሆኑ ተገልጿል።

ጉባኤው በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ፥ የዘንድሮዉ መሪ መልእክት ‘‘የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎትን ማስተዋወቅ እና በኮሮናቫይረስ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ ማጠናከር’’ የሚል ነዉ።

በጉባኤው በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማእረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ጨምሮ የተለያዩ የማይክሮ ፋይናንስ ፈጻሚዎች፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

የፋይናንስ ዘርፍ ባለሙያዎች እርስ በርስ ሐሳቦችንና ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ ጉባኤው መልካም እድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚታመን የኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ከበደ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.