Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመት እና አዋጆችን በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

ጨፌው በዛሬው እለት አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

ርዕሰ መስተዳድሩም በተለያየ ሃላፊነት ላይ የነበሩ ሰዎችን በዕጩነት አቅርበው አጸድቀዋል።

በዚህም፦

ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ – የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ

አቶ ፍቃዱ ተሰማ – የክልሉ መንግስት ተጠሪ

አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪ

አቶ ጀማል ከዲር ገልገዶ – የክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ልማት አስተዳደር ሃላፊ

አቶ ጌታቸው ባልቻ – የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ

አቶ ጂብሪል መሃመድ ሮባ – የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ

አቶ ቦጋለ ፈለቀ – የኦሮሚያ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ

አቶ ካሳሁን ጎፌ – የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ሀላፊ

አቶ ዳንኤል አሰፋ – የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

አቶ ከበደ ደሲሳ – የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

አቶ ተሾመ ግርማ – የኦሮሚያ ክልል ፀረ ሙስናና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚሽነር

አቶ ጋዘል አባሲመል አባጎራ – የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት

አቶ ጉዮ ዋሪዮ – የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል።

ጨፌው ከዚህ ባለፈም ለዞን እና ለወረዳ የቀረቡ የ65 ዳኞችን ሹመትም አጽድቋል።

በአዳነች አበበ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.