Fana: At a Speed of Life!

አማራ ክልል ከ42 ቢሊየን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰማራታቸው ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ42 ቢሊየን ብር በላይ ያሰመዘገቡ ባለሐብቶችን በኢንቨስትመንት ዘርፍ ማሰማራት መቻሉን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በደሴ ከተማ እየተገመገመ ሲሆን ፥ በዚህም ባለፉት 6 ወራት ፈቃድ የወሰዱት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ ከ87 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥራ እድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ ÷ምንም እንኳን አሸባሪ ቡድኑ በክልሉ በርካታ ዞኖች በሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ጉዳት ቢያደርስም ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን ተናግረዋል።

ገቢው የተገኘው ወደ ውጭ ከተላኩ ዘጠኝ ዓይነት ምርቶች መሆኑን ነው ኃላፊው የጠቆሙት፡፡

በቀጣይም ዘርፉን በማጠናከርና የወደሙትን ወደ ሥራ በማስገባት ተጨማሪ ገቢ ለማስገኘት በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

በክልሉ ከ850 በላይ ባለሀብቶች ሐብታቸውን እንዲያንቀሳቅሱ ማድረግ መቻሉም ተመልክቷል፡፡

በክልሉ ለተሠማሩ ባለሀብቶች ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ማቅረብ ተችሏል ያሉት ኃላፊው÷ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑም ጠቁመዋል።

የብድር አገልግሎት በመስጠት ረገድም ልማት ባንክን ከመሳሰሉ አበዳሪ ተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

በክልሉ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከ541 በላይ ፋብሪካዎች የወደሙ ሲሆን÷ እስካሁን 60 የሚሆኑት ወደ ሥራ መግባታቸው ተገልጿል፡፡

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.