Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ጥር 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ።
የክልሉ መንግስት ለአማራ ክልል ያደረገው ድጋፍ 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ነው፡፡
ድጋፉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ተገኝተው ለዞኑ አስተዳደር አስረክበዋል።
አቶ ሙኽታር ሳሊህ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ፥ በአሁኑ ወቅት የገጠሙ ችግሮችን በትብብርና በመደጋገፍ ማለፍ ወሳኝ ነው ብለዋዋል፡፡
በቀጣይ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሃላፊው አክለዋል፡፡
የክልሉ ህዝብና መንግስት ላደረገው ድጋፍ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጀማል አህመድ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሐረሪ ክልል መንግስት ኮሙኑኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.