Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ያበሎ ወረዳ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ እንዲወገድ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ያበሎ ወረዳ ከ800 ኪሎ ግራም በላይ የሆነ እና ግምቱ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚልቅ አደንዛዥ ዕፅ እንዲወገድ ተደረገ፡፡

በማቃጠል እንዲወገድ የተደረገው አደንዛዥ ዕፅ በተለያዩ ጊዜያት በቁጥጥር ስር የዋለ እንደሆነም ነው የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር ማሊቻ ጃርሶ የገለጹት፡፡

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከያበሎ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.