Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ወደ ሃገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጥሬ ገንዘብ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ እና የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
ዳያስፖራዎች ከተለያዩ ተቋማትና አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ እያደረጉ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ለብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እስካሁን ከ14 ሚሊየን 300 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
ድጋፉንም አሜሪካ ሳክራሜንቶ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከ12 ሚሊየን ብር በላይ፣ ጀርመን ኑረምበርግ የሚኖሩ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ እንዱሁም የሞጆ ከተማ ተወላጅ የሆኑ ዳያስፖራዎች አንድ ሚሊየን ብር አበርክተዋል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም ጀርመን ፍራንክፈርት የሚኖሩ የደቡብ ክልል ልማት ማህበር አባላት 100 ሺህ ብር ደጋፍ ማድረሀጋቸው ተገልጿል።
አሜሪካ ሜሪላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ 32 ነጥብ 37 ኩንታል አልሚ ምግብ መለገሳቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመገንባትና በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንሚቀጥሉ መናገራቸውን ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በምናለ ገበየሁ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.