Fana: At a Speed of Life!

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የክልሎች የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወር የጋራ እቅድ አፈፃፀሙን ከክልሎች ጋር እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የክልሎች የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወር የጋራ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር በከር ሻሌ፥ ባለድርሻ አካላት ተመጋጋቢ ስራዎችን በማሰባሰብ የዜጎች ስራ አጥነትን መቀነስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የዜጎችን የስራ አጥነት መጠን ለመቀነስ ስራና ሰራተኛን በሚገባ እንዲገናኙ ማድረግ፣ በክህሎትና ሙያ ላይ መስራትና የተፈጠረዉን የስራ እድልና ገበያን ማገናኘት እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያን እድገት በተያዘለት እቅድ ከግብ ለማድረስም ባለድርሻ አካላት የዜጎችን ጥቅም አስቀድመው በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ደግሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ናቸው።

በዘርፉ የተያዘው እቅድ እንዲሳካ በስራ ክህሎትና የተሻለ አስተሳሰብ ላይም መስራት እንደሚያስፈልግ ነዉ የገለጹት።

ያደጉ ሀገራት በእነዚህ ዘርፎች ላይ በመስራት እድገት ማስመዝገባቸውን ገልጸው፥ በኢትዮጵያ የዜጎችን ስራ አጥነት ለመቅረፍና ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ነው ያመለከቱት።

በቢቂላ ቱፋ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.