Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ሐይቅን 75 በመቶ ማፅዳት ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረማያ ከተማ በተሰራ የሴፍቲኔት ስራ የሐረማያ ሐይቅን 75 በመቶ ክፍል ከቆሻሻ ማፅዳት መቻሉ ተገለፀ።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሙለታ ቡሽራ እንደተናገሩት፥ የሴፍቲኔት መርሃ ግብሩን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ መጨረሻ በሐይቁ ዙሪያ ፅዳት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ዩኒቨርስቲው የሰው ሃይልና ቆሻሻ ማንሻ ትራክተሮችን በመመደብ ለሴፍቲኔት ስራው ድጋፍ የሰጠ ሲሆን ፥ በዚህም ዘመቻ 75 በመቶ የሐይቁን ክፍል ከተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቆሻሻ ማፅዳት መቻሉን አስታውቀዋል።
ባለፉት ሁለት ወራት ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው የሴፍቲኔት ስራ 363 አባወራዎች በከተማ ፅዳት ማሰማራት ተችሏል ተብሏል።
በዚህም በአማካኝነት ከ1 ሺህ 400 በላይ ቤተሰቦች ከእጅ ወደ አፍ የነበረውን ኑሮ ማሻሻል መቻሉም ነው የተገለፀው።
የከተማዋ የምግብ ዋስትናና የስራ ዕድል ፈጠራ አስተባባሪው አቶ ታጁ አህመድ፥ የሴፍቲኔት ስራው በዙር ለስራ አጦች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
በዚህም በመጀመሪያውና ለሶስት ዓመት በሚቆየው መርሃ ግብር የታቀፉት ተጠቃሚዎች ከሶስት ዓመት በኋላ አምራች ሃይል ሆነው እንዲወጡና የግል ንግድ እንዲጀምሩ የሚያስችላቸውን የተለያዩ የሙያ ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ በመርሃ ግብሩ መሠረት እንደሚሰጣቸው ጠቁመዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.