Fana: At a Speed of Life!

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልዑካን ቡድን  የዱባይ 2020 ኤክስፖን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣2014 (ኤፍ ቢሲ)  በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይፋዊ ጉብኝት እያደረገ ያለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የልዑካን ቡድን  የዱባይ 2020 ኤክስፖን ጎብኝቷል።

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፖው  የኢትዮጵያ እልፍኝ (Pavilion ) እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቾ  ማሳያ ቦታዎችን ተመልክቷል ።

በኤክስፖው በተዘጋጀ የኢትዮጵያ እልፍኝ (Pavilion ) የኢትዮጵያ የታሪክ፣ ባህል እና የኢንቨስትመንት እድሎች  እየተተዋወቁ ይገኛሉ።

በዱባይ 2020 ኤክስፖ ኢትዮጵያ የሰው ዘር እና የቡና መገኛ፣  የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሁም ምቹ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር  መሆኗን እያስተዋወቀች ትገኛለች።

ኤክስፖው ሊጠናቀቅ ሁለት ወራት የቀሩት ሲሆን፥ እስካሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጎብተውታል።

 

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.