Fana: At a Speed of Life!

ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በሆሳዕና ከተማ ግንባታቸው ለሚከናወኑ ተቋማት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በሆሳዕና ከተማ ግንባታቸው የሚከናወን የልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ተቋማት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
በሆሳዕና ከተማ በነበራቸው ፕሮግራም በከተማው ለሚገነቡ የመሰረተ ልማት ተቋማት የመሰረት ድንጋይም አኑረዋል።
የፊታውራሪ ጌጃ ገሪቦ መታሰቢያ ሐውልት ግንባታ፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ ስርዓት አካሂደዋል።
ባለ አምስት ወለል ህንጻ ያካተተው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይደረግበታል ነው የተባለው።
በሌላ በኩል የሆሳዕና ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክትንም ግንባታ ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ መቀመጡን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ 553 ሚሊየን ብር የሚፈጅ መሆኑም ተመላክቷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ የሊችጎጎ የልህቀት ማዕከል 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤትን መርቀው ከፍተዋል።
የተማሪዎችን መማሪያ እና የማደሪያ ክፍሎችን ህንጻዎች ተዘዋውረውም ተመልክተዋል።
የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ የግንባታ ወጪ በሀዲያ ልማት ማህበር የተሸፈነ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.