Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በሥድስት ወራት 28 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም 28 ቢሊየን ብር ገቢ መግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ገለፀ።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በግማሽ ዓመቱ 74 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱንም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያመለከቱት።

ኢትዮ ቴሌኮም የሥድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያደርግ ከታቀደው 86 ነጥብ 4 በመቶ ያህሉን ማሳካቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ኢትዮ – ቴሌኮም ዕቅዱን መቶ በመቶ ሊያሳካ ያልቻለው በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ግጭት አገልግሎት ይሰጥባቸው ከነበሩ ከ8 ሺህ በላይ አካባቢዎች ከ3 ሺህ 300 በላይ በሚሆኑት አገልግሎት በመቋረጡ መሆኑ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም ÷ በአማራ እና በአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ባለመስጠቱ እና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ምክንያትም ዕቅዱን ባሰበው ልክ አለማሳካቱ ተመልክቷል፡፡

ችግሩን ለመፍታትና ገቢውን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህ ሥድስት ወር ውስጥ 42 ምርት እና አገልግሎቶች ለደንበኞች መቅረባቸው የተነገረ ሲሆን በተጨማሪም 23 አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመጀመር ውጤት መገኘቱንም ነው ሥራ አሰፈጻሚዋ የተናገሩት፡፡

አዲስ ተግባራዊ ከተደረጉ እና በስፋት ሲሠሩ ከነበሩ ምርት እና አገልግሎቶች መካከል የ4G አገልግሎት፣ የአንድ ብር ጥቅል እና ቴሌ ብር ተጠቃሽ መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በቅድስት ተሥፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.