Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ ትኩረት የሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ የትውውቅ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትኩረት የሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች በህዝቡ ላይ በጣሉት ትልቅ ሸክም እና በማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ ለመቀነስ ሀገር አቀፍ ትኩረት የሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንደገለጹት፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነዚህን ትኩረት የሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች ለመቀልበስ የተቀናጀ ጥረት በፖሊሲ ደረጃ ብቻ ሳይሆን እስከታች ባሉ መዋቅሮች እና ትግበራ ደረጃዎች ምላሽ ሰጪ እና ተጠያቂነት ያለው ትኩረት እንዲሰጣቸው ይሠራል፡፡
 
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሰለሞን በበኩላቸው፥ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ሥርጭት የመግታትና በበሽታው የተጠቁ ወገኖች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ለጤና መዋቅሮች ብቻ የሚተዉ ባለመሆኑ ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለመተግበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.