Fana: At a Speed of Life!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የወደመው የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መልሶ ለማስጀመር የሚረዳ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የቤተ ሙከራ እቃዎች፣ ኮምፒውተሮች ፣ጠረጴዛዎች፣ አልጋዎች፣ ፍራሾች እና የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ነው ድጋፍ ያደረገው።

ዩኒቨርሲቲው ያደረገው የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ መላኩን የገለጹት የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ÷ ድጋፉ በሁለት ዙር እንደሚጓጓዝ ተናግረዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ዩኒቨርሲቲዎች መሰል ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

በወርቃአፈራው ያለው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.