Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ፣ ቻድ፣ ኮትዲቯር እና ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመካፈል የሶማሊያ፣ ቻድ፣ ኮትዲቯር እና ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
ማምሻውን አዲስ አበባ የገቡት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዲሰዒድ ሙሴ አሊ፣ የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመት ዜኔ ቸሪፍ፣ የካሜሮኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ቤላ ቤላ እና የኮትዲቯር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንዲያ ካሚስኮ ካማራ ናቸው።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ዋና ሹም አምባሳደር ፌይሰል አሊ አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.