Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት በሙስና ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ኤኔሪኬ ፔና ኔቶ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ ከሙስና በተጨማሪ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ስልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም ወንጀል መጠርጠራቸውን ምንጮችን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎም ፖሊስ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ፔና ኒየቶ ላይ ምርመራ ማካሄድ መጀመሩ ነው የተገለጸው።

የሜክሲኮ አቃቤ ህግ በበኩሉ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።

የወቅቱ ፕሬዚዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር በኩላቸው፥ ፔና ኔቶ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቶች ከስልጣን ሲወርዱ ለህግ ይቅረቡ ወይስ አይቅረቡ በሚለው ጉዳይ ላይ ፓርላማው ድምጽ ሊሰጥበት እንደሚችል ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.