Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሳዑዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሳዑዲ ዓረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢል ሳልማን ጋር በሪያድ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ ዓረቢያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ለውጥ አድንቀዋል።

ሞሃመድ ቢን ሳልማን በበኩላቸው በቀጠናው ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሀገራቱ በትብብር እና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ነው ያነሱት ።

ለዚህም የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤው ሀገራት ያላቸውን ትብብር ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሳዑዲ ዓረቢያ ከሚገኙ የተለየዩ የንግድ ማህበረሰቦች እና ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም ባለሃብቶች በኤርትራ የግብርና፣ የኢነርጅ፣ የአሳ ማስገር እና የማዕድን ልማት ዘርፎች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስም ባለሃብቶች በሀገሪቱ ለሚያደርጉት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.