Fana: At a Speed of Life!

ለ48 ወረዳዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ መላክ መጀመሩን የሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ ለ48 የክልሉ ወረዳዎች 198 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ሁለተኛ ዙር የአስቸኳይ ዕርዳታ መላክ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
የሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ለተጠቁ በ10 የክልሉ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 48 ወረዳዎች የሚኖሩ 197 ሺህ 928 ዜጎች ለሁለተኛ ዙር የሩዝ፣ ዘይት፣ ስኳር እንዲሁም ቴምርና ሌሎች የአልሚ ምግብ አይነቶች ያካተተ ዕርዳታ መላክ መጀመሩን ገልጿል።
በሌላ በኩል የምግብ ድጋፉ የሚጓጓዘው ከሶስት ማዕከላት ከጅግጅጋ፣ ጎዴይ እና ከዶሎ-አዶ የእርዳታ እህል መጋዘኖች እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ለሕፃናት፣ ለአራስና ነፍሰ ጡር እናቶች ማድረስ የታለመለትን የተመጣጠነ አስቸኳይ እርዳታ ምግቦች በአዳማ ከሚገኘው የፌደራል የምግብ ማከማቻ መጋዘን የተለያዩ አልሚ ምግብ ወደ ጎዴይና ዶሎ-አዶ ከተሞች እየተጓጓዙ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በጅግጅጋ ከተማ ከሚገኘው መጋዘን እንደሚያራግፉና ለተጠቃሚዎቹ የሚከፋፈል መሆኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.