Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመዘገብ እስካሁን 340 የውጭ አገራት ጋዜጠኞች አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመዘገብ እስካሁን 340 የውጭ አገራት ጋዜጠኞች አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለፀ።

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው በሚመክሩበት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት የሚዘግቡ 340 የውጭ አገራት ጋዜጠኞች አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ፥ የህብረቱን የመሪዎች ጉባኤ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በተለይም ከውጭ ለሚመጡ ጋዜጠኞች ከቪዛ ጀምሮ ባጅ መስጠትና ሌሎች ለመዘገብ የሚያስችሏቸውን ሁኔታዎች አመቻችተናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እስካሁን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ከ700 በላይ ጋዜጠኞች ለመዘገብ የሚያስችላቸውን ባጅ መውሰዳቸውን ገልጸው፥ በቀጣይ ቀናት ሌሎች ተጨማሪ የውጭ አገራት ጋዜጠኞችም ለተመሳሳይ ዓላማ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል ነው ያሉት።

የጋዜጠኞቹ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በአንዳንድ የምእራቡ ዓለም አገራት ሲራገብ የነበረውን የተሳሳተ መረጃ ተገንዝበው ያለውን ተጨባጭ እውነታ የሚዘግቡበት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.