Fana: At a Speed of Life!

በተጠቆሙት 42ቱ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ነገ የሕዝብ አስተያየት ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አግባቦች የተጠቆሙት 42ቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ነገ 8 ሰዓት ከ30 ላይ የሕዝብ አስተያየት እንደሚሰጥባቸው ተጠቆመ፡፡

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ተቀባይና አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ሔኖክ ስዩም÷ በሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኩ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ አካላት ፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ፣ የክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሲቪክ ማሕበራት ተወካዮች እንደሚገኙ ገልፀዋል ።

የ42ቱ እጩ ኮሚሽነሮች ስም እና የግል ሕይዎት ታሪክ (Profile) በምክር ቤቱ የፌስ ቡክ ገፅና ድረ-ገፅ ላይ እንደሚጫን ዶክተር ሔኖክ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.