Fana: At a Speed of Life!

የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል።

ለአህጉሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ጉባኤም ከሚሳተፉ የአፍሪካ መሪዎች የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ ዛሬ ምሽት ከልዑካን ቡድናቸው ጋር አዲስ አበባ ደርሰዋል።

ልኡኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የግብርና ሚኒስትር፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስትርና የጤና ሚኒስትርን ያካተተ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ናይጀሪያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን( የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት) አባል የሆነችው በፈረንጆቹ ግንቦት 25/1963 ነው ይላል የኢዜአ ዘገባ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.