Fana: At a Speed of Life!

የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል።

ለአህጉሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ በሚጠበቀው ቢዚህ ጉባኤም ከሚሳተፉ የአፍሪካ መሪዎች የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ ዛሬ ምሽት ከልዑካን ቡድናቸው ጋር አዲስ አበባ ደርሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ኮትዲቯር የአፍሪካ ህብረትን (የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን) የተቀላቀለችው በፈረንጆቹ ግንቦት 25/1963 ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.