Fana: At a Speed of Life!

ሰላምና መረጋጋትን በአፍሪካ ለማስፈን የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እንጠብቃለን – የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በኮቪድ-19 ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉና በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ ውሳኔዎችን እንጠብቃለን ሲሉ የጉባኤው ተሳታፊዎች ገለጹ።
ተሳታፊዎቹ በዚህ ጉባኤ በአፍሪካ የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ለኢዜአ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት በጉባኤው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የወጣቶች ስራ ፈጠራን ማጠናከር ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ፥ ይህም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍታት ያስችላል ብለዋል።
ውሳኔዎቹ አፍሪካ የሚያጋጥሟትን ችግሮች ተሻግራ ድል እንድታደርግ የሚያስችሉ ናቸው።
በአፍሪካ በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሌሎች ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መስራት አለብን ፤ በዚህ ጉበኤም ሰላምና መረጋጋትን በአፍሪካ ለማስፈን የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እንጠብቃለን ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.