Fana: At a Speed of Life!

ግምታቸው ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ቀናት ግምታቸው ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
 
የጽህፈት ቤቱ የኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን መሪ ኢንስፔክተር ዓለሙ ይመር እንደገለጹት÷ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት ጨለማን ተገን በማድረግ ወደ መሃል አገር ለማስገባት ሲሞከር ነው።
 
ጽህፈት ቤቱ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው እንቅስቃሴ ከምሥራቁ የአገሪቱ ክፍሎች ሲጓጓዙ የነበሩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግረዋል።
 
በዚህም መሰረት ጥር 25 ቀን 2014 ሁለት ከባድ የጭነት ተሸከርካሪዎች ግምታዊ ዋጋቸው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ልባሽ ጨርቆች፣አዳዲስ አልባሳትና መድሃኒት ጭነው ከሽኒሌ ዞን ሙሉ ወረዳ ወደ ገዋኔ ወረዳ በጉዞ ላይ እንዳሉ መያዛቸው ጠቁመዋል።
 
በተመሳሳይ ጥር 24 ቀን 2014 ምሽት 5 ሰዓት ጨለማን ተገን በማድረግ ሁለት የጭነት ተሸከርካሪዎች ግምታዊ ዋጋቸው ብር 13 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።
 
በኮንትሮባንድ ከተያዙት ዕቃዎችም ውስጥ መድሃኒት፣ሲጋራዎችና አልባሳት የሚገኙበት ሲሆን÷አሽከርካሪዎቹ ለጊዜው ከአካባቢው በመሰወራቸው ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.