Fana: At a Speed of Life!

የአርብቶ አደሩ አካባቢ ልማት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕቅድ አካል መሆን እንዳለበት ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከፓስቶራሊስት ፎረም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአርብቶ አደሩን አካባቢና የልዩ ድጋፍ ክልሎችን ልማት በሚመለከት የፓናል ውይይት አካሄደ።

የዘርፉ ምሁራን የተሳተፉበት ይህ ውይይት “አርብቶ አደርነት፣ የለውጥ ሂደትና የወደፊት አቅጣጫ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የአርብቶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

በመድረኩ አርብቶ አደሩ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚሰሩ የልማት ስራዎች የማህበረሰቡን ችግር በሚፈታና እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችን መሠረት ባደረገ መልኩ መሰራት እንዳለባቸው ተነስቷል።

አርብቶ አደሩ ወደ ዘመናዊ የእንስሳት ሃብት ልማት ገብቶ ተጠቃሚ እንዲሆንም ተገቢ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋልም ነው የተባለው።

አርብቶ አደሩ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ እንዲል በጥናት የተደገፈ እገዛ ማድረግ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕቅድ አካል መደረግ አለበት መባሉን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ  ያመላክታል ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.