Fana: At a Speed of Life!

በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የህወሓት የሽብር ቡድን እና ተባባሪዎቹ በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት በ2013 ዓ/ም ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ከጥር 24/2014 ጀምሮ ፈተናውን ሲወስዱ ቆይተዋል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ፥ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋርና በቤንሻንጉል ክልል በ189 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች የተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና የክልል ትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.